All news & tips
Health tip July 23, 2026

የቶንሲል ቀዶ ጥገና እና የልብ ሪህ (Rheumatic Heart Disease) ግንኙነት

የቶንሲል ቀዶ ጥገና እና የልብ ሪህ (Rheumatic Heart Disease) ግንኙነት

በኢትዮጵያ ብዙ ወላጆች "ቶንሲልን ካስወገድን የልብ ሪህ ይከላከላል?" ብለው ይጠይቃሉ።
መልሱ፦ አይደለም። ቶንሲል መወገድ ብቻውን የልብ ሪህን (Rheumatic Heart Disease) አይከላከልም፤ ስለዚህ የልብ ሪህን ለመከላከል ብቻ ተብሎ የቶንሲል ቀዶ ጥገና አይመከርም።

የልብ ሪህ በGroup A Streptococcus ባክቴሪያ የሚመጣ የጉሮሮ ኢንፌክሽን በአግባቡ ካልታከመ በኋላ ሊከሰት የሚችል ችግር ነው። ስለዚህ ዋናው መከላከያ የስትሬፕቶኮከስ ጉሮሮ ኢንፌክሽንን በጊዜው ማወቅና በተገቢው አንቲባዮቲክ ሙሉ ሕክምና መስጠት ነው። ነገር ግን ህፃኑ በተደጋጋሚ በስትሬፕቶኮከስ የሚከሰት የቶንሲል ኢንፌክሽን ካለበት፣ እና ለቶንሲል ቀዶ ጥገና የሚያስፈልጉ መደበኛ መስፈርቶችን የሚያሟላ ከሆነ፣ ቀዶ ጥገናው የኢንፌክሽን መደጋገምን በመቀነስ ጥቅም ሊያመጣ ይችላል። ሆኖም ይህ ማለት ቀዶ ጥገናው በራሱ የልብ ሪህን ይከላከላል ማለት አይደለም።

Have a question?

Call our reception — we're happy to help.

+251 99 495 0996
Back to News & Tips